ስለ እኛ
የሰላጃግር ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር አመሠራረት
ሰላጃግር ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በሎጀስቲክስ እና በአልባሳት ማምረት ተሰማርተው የነበሩ የሁለት የግል ድርጅቶች ጥምረት ውጤት ነው ። በጥቅምት 2019 እነዚህን ሁለት ድርጅቶች ማለትም ግርማ ከበደ ገምቴሳ የጉሙሩክ እና የዕቃ አስተላላፊ እና ነታንያ ዲዛይንን ( ሰላማዊት ታደለ የባህላዊ አልባሳት አምራች ) በማዋሃድ ሰላጃግር ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ተመሠረተ።
የተመሠረተበት መንገድ
ሰላጃግር ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ በቤተሰብ የተመሠረተ እና በቤተሰብ የሚተዳደር ኩባንያ ነው።
በሎጀስቲክስ ዘርፍ ፡ የጉምሩክ ማስተላለፍ ፣ የዕቃ ማስተላለፍ ፡ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ለአስመጪዎች እና ላኪዎች የምክር አገልግሎት እንሰጣለን ።
በጋርመንት ዘርፍ ፡ በዕውቅ ዲዛይነር በጥንቃቄ እና በጥራት የተሠሩ ለሕፃናት፣ ለወጣቶችና ለአዋቂዎች የሚሆኑ አልባሳት በማምርት ለገበያ እናቀርባለን። ምርቶቻችንም የሀገር ባሕል አልባሳት ፣ ቲሸርቶች፣ ፖሎ ሸርቶች፣ የስፖርት ትጥቆች፣ የውስጥ አልባሳት ፣ ዩኒፎርሞች አና ሌሎች አልባሳት ናቸው ።
ሚሊዮን ብር
መነሻ ካፒታል
ሰራተኞች
አሁን ያሉን ቋሚ ሰራተኞች


